Up next

እናትዋ ጎንደር | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Official Video) | SewMehon Films

7 Views· 02/27/23
admin
admin
1 Subscribers
1

እናትዋ ጎንደር ሙሉ የሙዚቃው ግጥም
በባልቴት ውበት ሁሌም ወይዘሪት
ማይነጥፍ ጅረት ጎህ ለነፃነት
ፈጣሪ ጦቢያን ሲከልላት
የምሰሶዋን ስም ጎንደር አላት
እንዳለች አለች ታተይ ሙሽሪት
ሒያጅና መጭን እንደታዘበች
እስኪ እህህ ልበል ጥቂት ባንች ቦታ
ታንጀትሽ ላይ ሆኘ ኸልብሽ በአንድ አፍታ
እንዴት ነው አዘዞ ጮማ በልቶ ጠጅ
ታንች የሚያደርሰኝ መግደርደርሽ እንጅ
የአባት የማረጉን ወግ ወጉን አዳብላ
አሳድጋኛለች እሹሩሩ ብላ
የምድር መዳኛው ታጠነ አርባራቱ
መሥዋአት አቅርቡ ስለት ለታቦቱ
ሴት አረሆ
አረ በፈጠረህ አረ እንዴው በሞቴ
እስኪ ተወኝ ባክህ ላታፅናናኝ እቴ
ይልቅስ ውሰደኝ ካለበት እትብቴ
መፅናኛየ እሷ ናት ልሒድ ወደ እናቴ
የዋልያ ቀንዱን መሥሎ ሹርባዋ
ሰልመም ብላ መጣች አረግ እናትዋ
ልቧም ካልፈቀደ ደስም ካላላት
በካሳ አትጨክንም በፋሲል በላት
በጎንደሮች መዳፍ ስጎርስ እዛም እዛም
ተመልሼ መጣሁ በእጄም ሳልጠቀም
ክፋ እስለምደሽኝ ጮማና ወርች
እናና ተጎዳሁ እኔ ስርቅ ካንች
የበሽታን ነገር ለሐኪም ይሰጡታል
የአጋንንትን ነገር ፀበል ይገቡታል
የጎንደርን ናፍቆት እንዴት ያረጉታል
እነ ቴቴ ጉርሻ አረ እንደምናችሁ
እነ ዋዋ ጉርሻ አረ እንደምናችሁ
ጉብ ጉብ አለብኝ አፈር ልብላላችሁ
የመሣፍንቱ እናት እቴቴ ማንአህሎሽ
ጉድ ጉድ በይልኝ ጥምቀት መጣሁልሽ
እንደ ህማማቱ የአንችው ፆመኛሽ
በባዶ እግሬ እምብርክክ የምሳለምሽ
መሠንቆ ተናገር ጀግንነቱን አውራ
አርግፎ የሚጥል ተሰማይ አሞራ
ድንበር ጠባቂ ነው በጠላቱ አይሞትም
መሣሪያው ደም መላሽ እንደ ታናሽ ወንድም

======================================

ድምፃዊ :- አስቻለው ፈጠነ (አርዲ)
ሙዚቃ ቅንብር :- እስራኤል መስፍን
ግጥም :- አስቻለው ፈጠነ አርዲ
የሴት አረሆ :- ጥሩወርቅ አየለ
ዜማ :- የህዝብና አስቻለው ፈጠነ አርዲ
መሰንቆ :- እንድሪስ ሐሰን
ክራር :- አስቻለው ፈጠነ አርዲ
ከበሮ :- ሀገረሰላም ሻፊ
አድማቂ :- መላኩ ታረቀኝ
ሲኒማቶግራፈር :- ፍስሀፅዮን ንብረት
ፕሮዳክሽን ዲዛይነር :- ሄለን ብዙነህ ( ቲና )
ፀሀፊና አዘጋጅና ፕሮዲዩሰር :- ሰውመሆን ይስማው
ሎካል ፕሮዲዩሰር :- ሀይሉ ፈንታሁን
ብርቧክስ ሪከርድስ

====================================

እናት ዓለም ጎንደር | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Official Video) | SewMehon Films
Enatwa Gonder |

Birbaux Records. SewMehon Films

Check Out New Ethiopian Entertainment Videos
by Subscribing @Birbaux Records.


#BirbauxRecords. #SewMehonFilms #EthiopianMusic #gonder

unauthorised use, distribution, and re-upload of this content is strictly prohibited

Copyright ©Birbaux Records. SewMehon Films

Show more

 0 Comments sort   Sort By


Up next